Tuesday, 28 October 2014
ዲሞክራሲ የግሪክ ቋንቋ መሆኑን የሚያምነው የወያኔ መንግስት ዲሞክራሲ ማለት እኔ የምለውን የሚከተል አድርግ የምለውን የሚያደርግ ነው እንጂ ካለኔ ፈቃድ ብሎገር ነኝ፣ የሚል ጋዜጠኛ ነኝ፣ ተቃዋሚ ነኝ የሚል እንዲህ አይነቱ በኔ አጠራር አሸባሪ ነው እነሱን የሚከተል የኔ ሊሆን አይገባውም
የሰው ልጅ በነጻነት በሚንቀሳበት በዚች ዓለም ላይ ለነጻነታቸው የሚታገሉ ንፁሀን ዜጐች መብታችን ይከበርልን የፈለግነውን የመምረጥ መብት ይኑረን የታሰሩ ወገኖቻችን ይፈቱልን ዲሞክራሲ መብታችን ይከበርልን ስላሉ ብቻ በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በተለያዩ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ትላንት አምንስቲ ባወጣዉ መግለጫ አምሰት ሺ የኦሮሞ ተወላጆች እስር ቤት ውስጥ እንደሚሰቃዩ በዘገባው አስረድቷል፥ እንግዲህ እነዚህ አምንስቲ እድሉን አግኝቶ የተመለከታቸው እስር ቤቶች ሲሆኑ መንግስት እንዳይጎበኙ የከለከላቸውን ስናስብ ምን ያህል እንደሆነ መገመት አያዳግትም።እንግዲህ ምንድነው ኢትዮጲያ የወደፊት ተስፉዋ ልጆቿን አስተምራና አስመርቃ ሁሉን በየፊናው በስራ አሰማርታ እየተንቀሳቀሰች ነገር ግን አምባገነኑ የወያኔ መንግስት የተማረው ሀይል እውቀቱ እየጎለበተ ሲመጣ መብቱንና ግዴታውን ሲያውቅ እንደ አንድ ዜጋ ስለ ሀገሩና ስለ ወገኑ ጬኸቱን ሲያሰማ ብዕሩን አንስቶ ሲፅፍ ጋዜጠኛው ሲዘግብ ዲሞክራሲ አለ እያለ ፖለቲከኛው ለምርጫ እራሱን ሲያዘጋጅ ዲሞክራሲ የግሪክ ቋንቋ መሆኑን የሚያምነው የወያኔ መንግስት ዲሞክራሲ ማለት እኔ የምለውን የሚከተል አድርግ የምለውን የሚያደርግ ነው እንጂ ካለኔ ፈቃድ ብሎገር ነኝ፣ የሚል ጋዜጠኛ ነኝ፣ ተቃዋሚ ነኝ የሚል እንዲህ አይነቱ በኔ አጠራር አሸባሪ ነው እነሱን የሚከተል የኔ ሊሆን አይገባውም በማለት በቅርቡ ብቻ አስራ ስምንት ጋዜጠኞች በእስር ቤት ሲገኙ ከዛ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ስርዐቱን በመሸሽ የተወለደበትን ሀገሩን ጥለው በጎረቤት ሀገር ሀገር እንደሌለው በየድንኳኑ ሲጠለል ይታያል ስለዚህ ስለኛ ነጻነት ነውና የሚሰቃዩት ሁላችንም በጋራ ከጎናቸው ለመቆም በጋራ እንነሳ አመሰግናለው። ተስፋዬ ወርዶፋ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment