በሶማሊያ በአንድ ታዋቂ ሆቴል ውስጥ ቦንድ ፈነዳ
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ጃዚራ ሆቴል ውስጥ በሁለት መኪኖች የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል። ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት በጠባቂዎች እና ፍንዳታውን ባደረሱት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።
በአሁኑ ፍንዳታ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። አልሸባብ አሁንም የደቡብ የሶማሊያ አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። የኢትዮጵያ ጦር አሁንም በሶማሊያ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Source. ESAT
No comments:
Post a Comment