Tuesday 16 September 2014

በዚህ ወቅት ሀገራችን ኦሮሚያ የተሰጣትን የይስሙላ አስተዳዳር እንኳ ተነጥቃ ቀጥተኛ ወታደራዊ አስተዳደር ስር ገብታለች። ገናና የተፈጥሮ ሃብት ብኖራትም እንኳ ህዝቧ ከልክ ባለፋ የባዕዳን ገዢዎች ብዝበዛ ና በፓርት የንግድ ተቋማት ተጽዕኖ ከዕኮኖሚ ዉድድር ዉጪ ሆነዋል። የድህነቱ መጠኑ እጅግ አስከፊ ነዉ። አርሶ አደሩ ሕዝባችን ከነባር ቄዬዉ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል። የትምህርት ሥርዓቱና የትምህርት አስተዳዳሩ የእነ አኪሊሉ ሃብተወልድ የቆያ ስዉር ሤራ አስፈጻሚ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም ሳቢያ የኦሮሞ ልጆች ዘመኑን የሚመጥን ዕዉቀት እንዳያገኙ ተደርጓል። ከዚያም አልፎ ት/ቤቶች ና የት/ት ተቋማት ወደ ወታደራዊ ቀጠና በመለወጣቸዉ ና በሕዝባችን ላይ ግልጽ ጦርናት በመታወጁ ፤ ስለህዝባቸዉ መብት የሚናገሩ ወጣቶችና ሕጻናት በገፍ እየተጨፈጨፉ ነዉ። ህዝባችን ባህሉን ፣ ቋንቋዉንና ታሪኩን እንዳያሳድግ ግልጽ አፈና ተደርጎበታል። ነጻ የፖለቲካ ና መህበራዊ ተቋማት (free political organizations and civic societies) እንዳይኖሩት ተከልክለዋል። ነባሮቹም እንዲዘጉ ና እንዲሰደዱ በመደረጉ በአጠቃላይ የህዝቡን ሕልዉና ለማጥፋት ከቁጥር ና ከዝርዝር በላይ የሆኑ ዘመቻዎች በመከፈታቸዉ ሕዝባችን ራስን የመከላከል አጸፋዊ እርምጃዎችን ለመዉሰድ ተገደዋል።

ሊነጋጋ ነዉና ንቃ! – ከቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነጻነት!

Posted: Fulbaana/September 16, 2014 · Finfinne Tribune | Gadaa.com | Comments
ሊነጋጋ ነዉና ንቃ!
መልዕክት ዐይኖቻችሁ ላልተገለጠ፦
1. የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለሆናችሁ የኦሮሞ ልጆች፣
2. የፖሊስ ሠራዊት አባላት ለሆናችሁ የኦሮሞ ልጆች እንዲሁም
3. ለኦህዴድ ካቢኔዎች ና ለደህንነት አባላት በሙሉ
በድሮ ዘመን አንድ ባለፀጋ ሰዉ ዝንጀሮዎችን በግዛቱ ሥር አሰባስቦ ያስተዳድር ነበር ይባላል። በመሆኑም በግዛቱ የዝንጀሮ ዐለቃ(the Monkeys Master) በሚል ቅጽል ይታወቅ ነበር። ታዲያ ጥዋት ጥዋት ዝንጀሮዎቹን ይሰበስብና ከማዶ ወዲያ ባለዉ ተራራ ላይ ወተዉ ከየዛፎቹና ቁጥቋጦች ላይ ፍራፍሬ ለቅመው እንዲያመጡ ያዛል። በትዕዛዙ መሠረት እያንዳንዱ ዝንጀሮ በዕለቱ ከሰበሰበዉ ፍራፍሬ ላይ ስሶዉን ለባለጠጋዉ ዐለቃ የመገበር ጽኑ ግዴታ አለበት። ይህንን ግዴታ የማይወጣ ካለ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህን ግዳጅ ተቆጣጥሮ የሚያስፈጽም ደግሞ አንዱን ጎበዝ ከመሃላቸዉ መርጦ ይሾማል። እናማ ዝንጀሮዎቹ በሙሉ በዚህ ክፉ ስርዓት በእጅጉ ይማረራሉ። ሆኖም ግን ዉስጥ ዉስጡን ከመጉረምረም ባለፋ ደፍሮ “በቃኝ!” የሚል ጎበዝ አልተገኘም ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሚጢጢ ዝንጀሮ በነገሩ ተገርማ ኖሮ፦
“ይህን ሁሉ የፍራፍሬ ተክል እኚህ ሰዉዬ ብቻቸዉን አልምቷል እንዴ ?” ስትል ያልተጠበቀ ጥያቄ ሰነዘረች።
“አረ በፊጹም! በተፈጥሮ የበቀለ ነዉ።” ስሉ ሌሎቹም በአግራሞት መለሱ።
“ታዲያ ያለእሳቸዉ ፈቃድ ፍራፍሬዉን መብላት አይቻለንም ማለት ነዋ!” ትንሿ ዝንጀሮ አከለች።
“እንዴታ! በደንብ እንችላለን እንጂ።” ሌሎቹ አሁንም በአግራሞት መለሱ።
“እንግዲያዉስ የሰዉዬዉ ባሪያ ሆነን መቅረታችን ስለምንድ ነዉ!” ብላ ሀሳቧን ሳትቋጭ የሌሎቹ ዓይን ተገለጠ። ነቁም። ቁጣቸዉም ተቀሰቀሳ። በዚያኑ ለልት ዐለቃቸዉን እንቅልፍ እስክ ወስዳቸዉ ጠብቀዉ ለአመታት የታጠረባቸዉን ግድግዳ ሰብረዉ ወጡ። ነጻነታቸዉን አወጁ። የተወሰዳባቸዉንም ምርኮ አስመለሱ። ከጥንት ጀምሮ ስበዘብዛቸዉ የነበረ ሰዉዬ በረሃብ ሞታ ይባላል። ይህ የጥንታዊ ቻይኖች ታዋቂ ምሳለያዊ ተረት (parable) ነዉ። ዓይናችሁ ሲገለጥ ብርሃንን ታያላችሁ። ክፉዎችንም ታወግዛላችሁ። ነጻነትንም ትሹታላችሁ። በትግላችሁም ኣርናት ይሆንላችኋል።
አሁን በሁለት ተቃራኒ መንታ ታርካዊ ጫፎች ላይ ነን። አንደኛዉ የፊጹም ጭለማ ተምሳሌት ፤ ሌላኛዉ የፊጹም ብርሃን መገለጫ ነዉ። አይቀሬዉ የታሪክ ክስተት እያተቃረባ ይገኛል። በትክክለኛዉ አጠራሩ ደግሞ የባርነት ፊጻሜ ና የነጻነት ጅማሮ።
በዚህ ወቅት ሀገራችን ኦሮሚያ የተሰጣትን የይስሙላ አስተዳዳር እንኳ ተነጥቃ ቀጥተኛ ወታደራዊ አስተዳደር ስር ገብታለች። ገናና የተፈጥሮ ሃብት ብኖራትም እንኳ ህዝቧ ከልክ ባለፋ የባዕዳን ገዢዎች ብዝበዛ ና በፓርት የንግድ ተቋማት ተጽዕኖ ከዕኮኖሚ ዉድድር ዉጪ ሆነዋል። የድህነቱ መጠኑ እጅግ አስከፊ ነዉ። አርሶ አደሩ ሕዝባችን ከነባር ቄዬዉ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል። የትምህርት ሥርዓቱና የትምህርት አስተዳዳሩ የእነ አኪሊሉ ሃብተወልድ የቆያ ስዉር ሤራ አስፈጻሚ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም ሳቢያ የኦሮሞ ልጆች ዘመኑን የሚመጥን ዕዉቀት እንዳያገኙ ተደርጓል። ከዚያም አልፎ ት/ቤቶች ና የት/ት ተቋማት ወደ ወታደራዊ ቀጠና በመለወጣቸዉ ና በሕዝባችን ላይ ግልጽ ጦርናት በመታወጁ ፤ ስለህዝባቸዉ መብት የሚናገሩ ወጣቶችና ሕጻናት በገፍ እየተጨፈጨፉ ነዉ። ህዝባችን ባህሉን ፣ ቋንቋዉንና ታሪኩን እንዳያሳድግ ግልጽ አፈና ተደርጎበታል። ነጻ የፖለቲካ ና መህበራዊ ተቋማት (free political organizations and civic societies) እንዳይኖሩት ተከልክለዋል። ነባሮቹም እንዲዘጉ ና እንዲሰደዱ በመደረጉ በአጠቃላይ የህዝቡን ሕልዉና ለማጥፋት ከቁጥር ና ከዝርዝር በላይ የሆኑ ዘመቻዎች በመከፈታቸዉ ሕዝባችን ራስን የመከላከል አጸፋዊ እርምጃዎችን ለመዉሰድ ተገደዋል።
በመሆኑም ይህንኑን ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት ከጨለማ ሥርዓት ፋልሣችሁ ወደ ነጻነት ብርሃን ለተቀላቀላችሁ ና በመቀላቀል ላይ ለሚትገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፖሊስ ሠራዊት አባላት እንዲሁም የኦህዴድ ካቢኔዎች ና ለደህንነት አባላት ለሆናችሁ ወገኖች ለወሰዳችሁት አኩሪ እርምጃ በቅድሚያ ላቅ ያላ ወገናዊ ምስጋና እናቀርባለን። በአንጻሩ ደግሞ ዓይናቸዉ ባለመገለጡ አሁንም ለተወራራሽ ዓምባገነን ገዢዎች አንገታችሁን ደፍታችሁ በማገልገል ላይ ለሚትገኙ ለምስኪን ወገኖቻችን ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን ለማዳን ወደ ሕዝባዊ ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ በዚህች በመጨረሻ ሠዓት ይህ ብሔራዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል። ልነጋጋ ነዉና ንቃ!
ድል ለኦሮም ሕዝብ!
ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ለነጻነት!
September 16, 2014

No comments:

Post a Comment