Friday 5 June 2015

በኖርዌይ የስደተኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ለብዙ ዓመታት መቆየቱ ታወሳል፡፡ ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ መለስ ብሎ አጀማመሩንና አሁን የላበትን ደረጃ በዝርዝር ማየቱ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በግልም ሆነ በጋራ ተነሳስቶ ታላላቅ ወገናዊና ሰብኣዊ ጉዳዮችን መተግበር እንደሚቻልም የሚሰጠው ትልቅ ትምህርት አለና ዝርዝሩ እነሆ... እ.አ.አ. በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የኖርዌይ መንግሥት በኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች ላይ አንድ ያልተጠበቀ እርምጃ ወሰደ፡፡ ቀደም ሲል ያቀረቡት የመኖሪያ ፍቃድ ጥያቄ በተደጋጋሚ ተቀባይነት ያላገኘላቸውና ባገኙት የሥራ ፈቃድ ሠርተው እራሳችውንና ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በድንገት የዚህ ችግር ሰለባ ሆኑ፡፡ ቤትና መኪናን የመሳሰሉ ንብረቶች አፍርተው፣ ልጆች ወልደው (ሕጋዊ ጋብቻ ግን ተከልክለው) እየሠሩ ይኖሩ የነበሩ በሙሉ ወደ ስደተኖች ካምፕ እንዲገቡ ተገደዱ፡፡ ይህ ድንገቴና ያልተጠበቀ ዱብዳ በኖርዌይ አገር ለእስታቫንገሩ ነዋሪና የእስታቫንገር ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ የትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለሆነው ለዶ/ር ግሩም ዘለቀ የሚዋጥ አልሆነም፡፡

የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ -በአበራ ለማ የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም ይታወሳል፡፡ http://www.airecentre.org/pages/who-we-are.html#sthash.DNrjajaU.dpuf የኦስሎው አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎትና ጉዳያቸው በናሙናነት የታየላቸው የዘጠኙ ስደተኞች ስም ዝርዝር ይህ መቀመጫውን በፈረንሳይ አገር እስትራስቡርግ ከተማ ያደረገው የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት በመጨረሻ ላይ ጉዳዩን መርምሮ በሰጠው ብይን፤ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶች ብይን ከሰጡባቸው የስደተኖች ጉዳዮች መካከል፣ ከ60-70 በመቶ የሚሆኑት ተመሳሳይ እንደሆኑ ተችቶ፣ ተመሳሳይ ብይን የተሰጠባቸውን ነገር ግን ተመሳሳይ የጥገኝነት ጥያቄ መንስዔ ጭብጥ የሌላቸውን ጉዳዮች ለናሙና ያህል መርጦ በአስራ አንዱ ላይ እንዳዲስ ብይን እንዲሰጥበት ለኖርዌይ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት የ500ዎቹን የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢ ባለጉዳዮችን ማንነትና ችግሮች መርምሮ እንደደረሰበትም ከሆነ ከ500ዎቹ ባለጉዳዮች መካከል 340ዎቹ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጆች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ከአስራ አንዱ የናሙና ተመራጮች መካከል አብዛኞቹን የኦሮሞ ተወላጆች ባለጉዳዮች ሲያደርግ፣ ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ ቀደም ሲል ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙ በመሆናቸው ጉዳያቸው ሲሰረዝ፣ የዘጠኙ አቤቱታ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ቀርቦ፤ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ይግባኝ ሰሚ ባለሥልጣን (UNE- Utlendingsnemnda) ጠበቆች ጋር 2 ሲከራከሩበት መሰንበታቸውን እችሎቱ ላይ ተገኝተን ባይን ምስክርነት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ሲያከራክር ከሰነበተ በኋላ፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ብይን ለመስጠት ወስኖ ችሎቱ ተነስቷል፡፡ በኖርዌይ የስደተኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ለብዙ ዓመታት መቆየቱ ታወሳል፡፡ ይህን ጉዳይ ወደ ኋላ መለስ ብሎ አጀማመሩንና አሁን የላበትን ደረጃ በዝርዝር ማየቱ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በግልም ሆነ በጋራ ተነሳስቶ ታላላቅ ወገናዊና ሰብኣዊ ጉዳዮችን መተግበር እንደሚቻልም የሚሰጠው ትልቅ ትምህርት አለና ዝርዝሩ እነሆ... እ.አ.አ. በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የኖርዌይ መንግሥት በኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች ላይ አንድ ያልተጠበቀ እርምጃ ወሰደ፡፡ ቀደም ሲል ያቀረቡት የመኖሪያ ፍቃድ ጥያቄ በተደጋጋሚ ተቀባይነት ያላገኘላቸውና ባገኙት የሥራ ፈቃድ ሠርተው እራሳችውንና ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በድንገት የዚህ ችግር ሰለባ ሆኑ፡፡ ቤትና መኪናን የመሳሰሉ ንብረቶች አፍርተው፣ ልጆች ወልደው (ሕጋዊ ጋብቻ ግን ተከልክለው) እየሠሩ ይኖሩ የነበሩ በሙሉ ወደ ስደተኖች ካምፕ እንዲገቡ ተገደዱ፡፡ ይህ ድንገቴና ያልተጠበቀ ዱብዳ በኖርዌይ አገር ለእስታቫንገሩ ነዋሪና የእስታቫንገር ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ የትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለሆነው ለዶ/ር ግሩም ዘለቀ የሚዋጥ አልሆነም፡፡ በማህበራዊ ሕይወት የእለት በእለት ግንኙነት አብሯችው በደስታ ይኖሩ የነበሩ ያገሩ ልጆች ሲቸገሩ ማየቱ ሰላሙን ነሳውና ”ምን ይደረግ? ምን መላ ይበጅ?...” እያለ ማብሰልሰሉን ተያያዘው፡፡ ለጊዜውም አንድ መላ ታየው፡፡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን፣ የኖርዌይ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የሃይማኖት ድርጅት ተወካዮችን፣ ትውልደ ኖርዌጂያንና ኢትዮጵያውያን ያገሪቱን ዜጎችና ወዘተ... ያካተተ ጉባዔ በእስታቫንግር ከተማ የባሕል ማእከል እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2011 እንዲካሄድ አደረገ፡፡ በዚህ ጉባዔ ላይ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ተከልክለው በካምፕ ተወስነው እንዲሰቃዩና፤ ብሎም ወዳገራቸው ተገደው እንዲመለሱ ሊደረጉ ስለተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጠያቂዎች ችግር በሰፊው ተወሳ፡፡ ዶ/ር ግሩም ዘለቀና ታዋቂው የእስታቫንገሩ ጠበቃ በንት ኤንደርሰን ይህ ጉባዔም አንድ እልባት ላይ ደርሶና ቀጣዩ መራራ ትግል መከተል ያለበትን አቅጣጫ አመላክቶ ተበተነ፡፡ በውሳኔውም መሰረት የጥገኝነት ጠያቂዎቹ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በግል ጠበቆች አማካኝነት ይግባኝ እንዲጠየቅበትና ተገዶ ወዳገር ቤት የመመለሱም ጉዳይ ተግባራዊ እንዳይሆን እግድ የሚጣልበት ሁናቴ እንዲፈጠር መርሃ ግብር ተነደፈ፡፡ ይህ በዶ/ር ግሩም የግል ተነሳሽነት የተጀመረው ጉዳይ በጉባዔው ውሳኔ መሰረት በመጀመሪያ ሁነኛ የግል ጠበቆችን እማግኘቱ ላይ አተኮረ፡፡ እናም ዶ/ር ግሩም በእስታቫንገር ከተማ ውስጥ የሚገኘውን ትልቁን የጥብቅና ሥራ ቢሮ ኢቢቲን (EBT – Advokatfirma Endersen Brygfjeld Torall AS) ለትብብሩ ጠየቀ፡፡ ኢቢቲም ተገቢው የጥብቅና አገልግሎት ሂሳብ ከተከፈለው፣ ጉዳዩን ወደ ችሎት ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸለት፡፡ ዶ/ር ግሩም ተደሰተ፡፡ ”ግን የክፍያው ገንዘብ ከየት ይመጣ ይሆን ?...” አያለ መጨነቁ አልቀረም፡፡ አዎን አንድ መላ መጣለት፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና፣ ለሰው ደራሽ ሰው ነውና፤ ለባእዱም ለዘመዱም ጉዳዩን አድርሶ የሰው አድኑ ዘመቻ 3 እንዲካሄድ ተለመ፡፡ እናም ይህንን የገንዘብ ማሰባሰቡን ዘመቻ የሚያግዝና የሚያስተባብር አንድ ሕጋዊ ደርጅት እንዲቋቋም አደረገ፡፡ ድርጅቱም ”ፍትህ ለፖለቲካ ስደተኞች” ( RIA – Rettferdighet i Asylpolitikken) የተሰኘ ሆነ፡፡ ይህ ድርጅት ትውልደ ኖርዌጂያን የሆኑና አንድም ኢትዮጵያዊ የሌለበት ባለሰባት ሰዎች ቦርድ አቋቁሞ እስከዛሬ ድረስ ሥራውን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ቦርዱ በመዋጮ የተሰባሰበውን ገንዘብ ለጠበቆች ሥራ ወጪ እያደረገና ተጨማሪ እርዳታም እንዲገኝ የሚያስተባብር ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ በኖርዌይ የስደተኝነት ጥያቄ አቅራቢዎች ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እልባት ሳያገኝ አንድ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ፡፡ ይሄውም ኖርዌይ ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች በተለየ መልኩ የስደተኞቹን ጥይቄ ለመመልከት መንቀሳቀሷ ነው፡፡ ይሄውም የስደተኝነት ጥያቄ አቅርበው የመኖሪያም ሆነ የሥራ ፍቃድ የከለከለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወዳገራቸው ተገደው እንዲመለሱ፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት መፈራረሟ ነው፡፡ ይህ በቀድሞዋ የኖርዌይ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ግሬቴ ፋሬሞ አማካኝነት በጃኑዋሪ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈረመው ያስገድዶ መመለስ ስምምነት ታላቅ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ http://atelierpopulaire.no/ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኢትዮጵያውያንን፣ ትውልደ ኖርዌጂያንና የሌሎች አገር ፍትህ ናፋቂያንን ሁሉ ባንድ ጎራ አሰልፎ፣ የኖርዌይን መንግሥት የሚፈታተን የዘመኑ አቢይ አጀንዳ ሆነ፡፡ ቀስ በቀስም ከኖርዌይ ውጭ ያሉትንም ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ግለሰቦችንና ተቋማትን ሁሉ ስሜት የሚስብ ጉዳይ ሆነ፡፡ ሆኖም የኖርዌይ መንግሥት ባቋሙ በመጽናቱ፣ እ.አ.አ. ከማርች 15 ቀን 2012 ጀምሮ ፍቃድ የሌለው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁሉ እየተገደደ ካገር እንዲባረር መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የተጠለሉ ሁሉ ከካምፑ ተባረሩ፡፡ ብዙ ስደተኞች ኦስሎ በሚገኘው ዶም ሺርከን በሚባለው ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ካርቱን እያነጠፉ ሊጠለሉ ተገደዱ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ወደ እስዊድን ለዳግም ስደት ተዳረጉ፡፡ ብዙ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች ውስጥ ተካሄዱ፡፡ እሱም በዛ ያለው ፓሊስ በኃይል እያስገደደ ስደተኞቹን ከቤተክርስቲያን ደጃፍ እንዲባረሩ አደረገ፡፡ የኢትዮጵያውያን ሰቆቃና እምባ ወደር አቻ አጣ፡፡ ምን ቢደረግ ይሻላል የሚለው ጥያቄ አሁንም ግዘፍ ነሳ፡፡ ባንጻሩም ጉዳዩን በበላይነት የሚያስተባብሩት የሚኒስትር ግሬቴ የኋላ ታሪክ ምንነትም እየተነሳ መተቸት ተጀመረ፡፡ ይሄውም ከኢትዮጵያ ስደተኖች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሴትዮዋ የነበራቸውን አሻራ የሚዳስስ ነው፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነበር... ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን አስገድዶ ወዳገር ቤት ለመመለስ ከተዘጋጀው ሰነድ መካከል ቅጥያ 3 ዶ/ር ግሩም እንዳጫወተኝ ከሆነ፣ የሠራተኛ ፓርቲዋ ሚኒስትር ግሬቴ በ90ዎቹ አሠርት አጋማሽ ላይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ አንዲት ባለሁለት ሕጻናት እናት ኢትዮጵያዊት በሁለት የኖርዌይ ፖሊስ አጃቢነት ተገዳ ወደ ኢትዮጵያ እንድትመለስ ትደረጋለች፡፡ በፖሊሶቹ እንደታጀበች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ስትደርስም፣ እሪ ብላ ተጮሃለች፣ ታለቅሳለች፡፡ የቦሌ የኢሚግሬሽን ሠራተኞችም ለምን እንደምታለቅስ ሲጠይቋት፣ አስገድደው እየመለሷት እንደሆነ ታስረዳለች፡፡ ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ መታወቂያም እንድታሳይ ስትጠየቅ፣ አንዳችም የማንነትዋ ማረጋገጫ ሰነድ በእጅዋ ላይ እንደሌለ ሲረዱ እሷንና ልጆቿን ላለመቀበል አሻፈረን ይላሉ፡፡ በአደራ ሊያደርሷት አብሯት የተጓዙት 4 የኖርዌይ ፖሊሶች ያልጠበቁት ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡ ሴትዮዋንና ልጇቿን ይዘው ወደ ኖርዌይ እንዲመለሱ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ ኢሚግሬሽንም የፖሊሶቹን ፓስፖርት ነጥቆ ሴትዮዋንና ልጇቿን ይዘው ሼራተን አዲስ ሆቴል እንዲያርፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ከአሥራ አምስት ቀናት ፈታኝ ዲፕሎማሲያዊ ፍጭት በኋላ ሴትዮዋንና ልጆችዋን ይዘው ወደ ኖርዌይ እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ይደረሳል፡፡ ሂልተን አዲስም ፖሊሶቹ፣ ሴትዮዋና ልጆቿ ያለባቸውን የ350,000.00 ብር ወጪ አስከፍሎ ይለቃቸዋል፡፡ ፖሊሶቹ ሴትዮዋንና ልጆቿን ይዘው ወደ ኖርዌይ ሲመለሱ ወሬው ጋዜጠኞች ጆሮ ይደርስና በሚኒስትር ግሬቴና መሥሪያ ቤታቸው ላይ ከፍተኛ ወቀሳና ሂስ ያስከትላል፡፡ ከዚያ ወዲህ እንዲህ ዓይነቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስገድዶ የመመለሱ ጉዳይ ለብዙ ዓመታት ተቋርጦ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ሚኒስትር ግሬቴ በሌላ ጥፋት ተባረው ወደነበረበት ሥልጣናቸው ከአሠርታት ዓመታት በኋላ ሲመለሱ፣ ይህን አዲስ ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በማድረግ ሊተገብሩት ሲጣጣሩ ነው፤ የዶ/ር ግሩም ያላሰለሰ የጥረት ውጤት የሆነው ያውሮፓው የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ሕግ እገዳ ያቆማቸው፡፡ ዝርዘሩን ከታች እንመለስበታለን፡፡ ለጠበቆች ስለሚከፈለው የገንዘብ መዋጮ ማስተባበር ጉዳይ ስንመለስ፣ ዶ/ር ግሩምና RIA የነደፉት መርሃ ግብር ውጤታማ የሆነ ነበር፡፡ ”ፍትህ በኖርዌይ ላሉ ኢትዮጵያውያን” (Justice for Ethiopians in Norway) የሚል ድረ ገጽና የፓልቶክ ክፍል ተከፍቶ፣ ጉዳያቸው በእስታቫንገሮቹ ጠበቆች በኩል እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉ የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁሉ እንዲያመለክቱ ተጋበዙ፡፡ ወደ 500 ያህሎች ተመዝግበው፣ ከፍተኛ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻው ተጀመረ፡፡ በግለሰብ ደረጃ በነፍስ ወከፍ አቅም በፈቀደ ከተካሄደው መዋጮ ሌላ፤ ዶ/ር ግሩም በራሱ ወጪና ኪሳራ እየተንቀሳቀሰ በኢትዮጵያውያንና ኖርዌጂያን ተባባሪዎች እየታገዘ፣ በስምንት የኖርዌይ ከተሞች የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ በወጉ እንዲፈጸም አድርጓል፡፡ መዋጮ የተሰባሰበባቸው ከተሞችም፣ እስታቫንገር፣ ኦስሎ፣ በርገን፣ ትሮንድሃይም፣ ቡዶ፣ ትሮምሶ፣ ክርስቲያንሳንድና አስቴንሻር ናቸው፡፡ ባጠቃላይ ወደ 600,000.00 ኖርዌጂያን ክሮነር (በግምት ወደ 109,000.00 ዶላር) ሊሰባሰብ እንደቻለ ዶ/ር ግሩም ይናገራል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ በኦስሎ ከተማ ያንድ ምሽት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ብቻ 123,000.00 ክሮነር ለሲባሰብ ችሏል፡፡ በተጨማሪም ከኖርዌይ ቤተክርስቲያናት 100,000.00 ክሮነር፣ አንዲት 60 ዓመታቸውን ያከበሩ ኖርዌጂያዊት የቤተክርስቲያን አገልጋይ በስጦታ የተበረከተላቸውን 36,000.00 ክሮነር ለዚህ በጎ ተግባር ሲያበረክቱ፣ አንዲት ኤርትራዊት ሴትም 5000.00 ክሮነር እንደለገሱ ዶ/ር ግሩም በምስጋና ያስታውሳል፡፡ ለጠበቃ እንዲከፈል ከተደረጉ መዋጮዎች አንዱ ናሙና ዶ/ር ግሩምና ለዚህ ሰናይ ተግባር በዙሪያው የተሰባሰቡ ወገኖች ሁሉ፣ ይህ ገንዘብ መሰባሰቡን እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ፣ በ”ፍትህ ለፖለቲካ ስደተኞች” ( RIA – Rettferdighet i Asylpolitikken) ድርጅት አማካኝነት ለኢቢቲ (EBT – Advokatfirma Endersen Brygfjeld Torall AS) ጠበቆች ተፈላጊውን ክፍያ ፈጽመው እ.አ.አ. አፕሪል 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ጉዳዩን በይፋ ፍትህ እንዲጠይቁበት ኃላፊነት ተሰጣቸው፡፡ እነዚህ በሳልና በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ልምድ ያላቸው ጠበቆች፤ ጉዳዩን አጣድፈው ለኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አቀረቡ፡፡ በኖርዌይ ታሪክ ውስጥ 500 ሰዎች ተባብረው የኖርዌይን መንግሥት ሲከሱ የመጀመሪያው ዓይነት በመሆኑ፣ ይበልጥ የብዙዎችን ወገኖች ስሜት ሳበ፡፡ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ክርክሩና ውይይቱ ሁሉ ተጋጋለ፡፡ ዶ/ር ግሩምና የፍትህ ሚኒስትሯ ግሬቴ ፋሬሞ ባገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን (NRK TV) ላይ በእንግድነት ቀርበው ከፍተኛ ክርክር አካሂደዋል፡፡ አን ማግሪት አውስቴና በኖርዌይ ለስደተኞች የቆመ ድርጅት ዋና ጸሐፊም (NOAS – Norwegian Organization for Asylem Seekers http://www.noas.no/) ከሚኒስትር ግሬቴ ጋር ረዥም ሰዓታት የፈጀ የድረ ገጽ ላይ ክርክርና ምልልስ አካሂደዋል፡፡ 5 ታዲያ ለኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ይግባኝና አቤቱታ በግንቦት 2012 መጨረሻ ላይ ወድቅ ተደረገ፡፡ ፍርድ ቤቱ የሰጠውም ሰበብ፣ ጉዳያቸው የተናጠል የጥገኝነት ጥያቄ ስለነበር 500 ሰዎች ተሰባስበው በጋራ መክሰስ አይችሉም የሚል ነበር፡፡ ተስፋ የማይቆርጡት የእስታቫንገሮቹ ጠበቆች ይግባኛቸውን ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት (Lagmannsrett) ያቀረቡት ወዲያው ነበር፡፡ ይህ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም በበኩሉ አቤቱታውን ውድቅ አድርጎ፣ የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጸና፡፡ የእስታቫንገሮቹ ጠበቆች አሁንም አልተበገሩም፡፡ አቤቱታቸውን ለኖርዌይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወዲያቀው አቀረቡ፡፡ ሆኖም የኖርዌይ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ምላሽ ያው አሉታዊ በመሆኑ፣ ዶ/ር ግሩምና ጠበቆቹ በቀጣዩ ስለሚወስዱት እርምጃ ቆም ብለው ማውጠንጠን ነበረባቸውና ብዙ ተወያዩበት፡፡ እናም ዶ/ር ግሩም ለዶክትሬት ድግሪው ሎንዶን ሂዶ ሲያጠና ስለሚያውቀው በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የጥብቅና አገልግሎት ስለሚሰጠው መንግሥታዊ .ያልሆነ ድርጅት ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) እርዳታ አሰበ፡፡ ወዲያውንም ከድርጅቱ ጋር ግንኙነት ፈጠረ፡፡ በጋራ በደረሱበትም ስምምምነት መሠረት ከእስታቫንገሩ የኢቢቲ ጠበቆች ደርጅት ጋር ተባብረው ጉዳዩን ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት እንዲያቀርቡት እ.አ.አ. በሰኔ ወር 2012 ዓ.ም. ጉዳዩ ወደነሱ ተመራ፡፡ ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe)ም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረትን በመስጠት እ.አ.አ. በሰብቴምበር 2012 ዓ.ም. አቤቱታውን ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት አቀረበው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤትም የቀረበለትን የ500 ኢትዮጵያውያን የጥገኝነት ጥያቄ ረዥም ጊዜ ወስዶ ሲመረምር ከቆየ በኋላ፣ በዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ እንደተገለጠው ሁሉ ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡ የእሰታቫንገሮቹ ሦስቱ ጠበቆች (ከግራ ወደ ቀኝ) ቢዮርን ኢንገ ዎገ፣ በንት ኤንደርሰን፣ ሼል ኤም ብሪግፊዬልድና ጸሐፊው በችሎቱ ውስጥ ኢቢቲን (EBT – Advokatfirma Endersen Brygfjeld Torall AS) እና ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) ተባብረው ለአውሮፓ ሕብረት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ኖርዌይ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፕሮቶኮል ቁጥር 4ን ጥሳ ከኢትዮጵያ ጋር ስደተኞችን አሰገድዶ የመመለስ ሰምምነት ማድረግ እንደማይገባት የሚጠይቅ ነው፡፡ ፕሮቶኮል 4 እንደሚደነግገው ከሆነ፣ ሰዎችን በጅምላ ካንድ አገር ወደ ሌላ አገር አስገድዶ ማባረርን አጥብቆ ይከለክላል፡፡ በአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድንጋጌ አንቀጽ 39 መሰረት ደግሞ ሰዎች በሕይወታቸው ላይ አደጋና ስቃይ ሊያደርስ ወደሚችል አገር አስገድዶ መውሰድ እንደማይቻል የሚከለክል ሕግ አለ፡፡ በዚህም መሰረት ጠበቆቹ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤትን የጠየቁት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ችግር ያለበት በመሆኑ፣ ኖርዌይ እንዲህ ያለ ስምምነት ልታደርግ አትችልም የሚል እንደሆነ፣ ጉዳዩን የያዙት ሦስቱ ጠበቆች ለጸሐፊው አብራርተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ይህን ጥያቄ ተቀብሎ፤ ጉዳዩ በድጋሜ በኖርዌይ ፍርድ ቤቶች እስኪታይ ድረስ፣ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ተገደው ወዳገራቸው እንዳይመለሱ ወስኗል፡፡ በተጨማሪም የኖርዌይ ፍርድ ቤቶች በኖርዌይ መንግሥት ጠቅላላ ወጪና ኪሳራ የተመረጡትን ዘጠኝ ወካይ ባለጉዳዮች አቤቱታ እንዲመለከት ተበይኖበታል፡፡ በዚህ ውሳኔ መንስዔም ከዚያ ወዲህ ኖርዌይ ከማናቸውም አገሮች ጋር እንዲህ ያለ ስደተኞችን አስገድዶ የመመለስ ስምምነት ማድረግ እንዳቆመች ጠበቆቹ ያስረዳሉ፡፡ ይሄው የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት 6 በሰጠው ተጨማሪ ብይንም፤ ከ60-70 የሚሆኑት የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳያቸው በኖርዌይ ፍርድ ቤቶች የወደቀበት ምክንያት ተመሳሳይ መሆኑ እንዳላስደሰተው ጠቅሶ፣ ጉዳያቸው እንደገና በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲታይላቸው ብይን ሊሰጥ ችሏል፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ይህንን ጉዳይ ረዥም ጊዜ ወስዶ በሚመረምርበት ወቅት ሰለጉዳዩ እዚህ ኖርዌይ ውስጥ ይካሄድ የነበረውን ዝርዝር ጉዳይ ዶ/ር ግሩም ባንክሮ ያስታውሳል፡፡ ”ፍትህ ለፖለቲካ ስደተኞች” ( RIA – Rettferdighet i Asylpolitikken) በሚል መጠሪያ የተቋቋመው ድርጅት ያስተባበራቸው ግለሰቦች የ100 ስደተኞች ጉዳይ በኖርዌይ የኢሚግሬሽን ይግባኝ ሰሚ ባለሥልጣን (UNE- Utlendings nemnda) እንዲታይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ከነዚህም አቤቱታ ከቀረበላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኖች መካከል ቤተሰቦች ያላቸው ሁሉ ጉዳያቸው በድጋሜ እንዲታይላቸው እንደተደረገ ዶ/ር ግሩም አመልክቷል፡፡ በሌላም በኩል ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው ሆይረ (Conservative Party of Norway - Høyre (H) የተባለው የቀኝ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በትረ ሥልጣንን ከጨበጠ በኋላ፣ በዚህ በኢትዮጵያ ስደተኖች ጉዳይ ላይ የወሰዳቸው አንዳንድ እርምጃዎች እንዳሉ ዶ/ር ግሩም ያሰምርበታል፡፡ ሆይረ የነዶ/ር ግሩምን መሰረታዊ ጥያቄዎች ተንተርሶ ሁለት አበይት መመሪያዎች በሥራ እንዲውሉ አድርጓል፡፡ የመጀመሪያው ኖርዌይ ውስጥ ከሦስት ዓመታት በላይ የኖሩ ማናቸውም የጥገኝነት ጥያቄ አቅራቢ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ከነቤተሰቦቻቸው ምህረትን እንዲያገኙ የሚደነግገው ሕግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከማናቸውም አገር የመጡና ከአራት ዓመት ተኩል በላይ ኖርዌይ ውስጥ የኖሩ ስደተኛ ሕጻናት፣ ጉዳያቸው በልዩ ጉዳይነት ታይቶላቸው ውሳኔ ሳይሰጥበት ካገር እንዳይባረሩ የደነገገው ሕግ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ እነዚሁ ሕጻነት ከአራት ዓመት ተኩል በላይ እዚህ ኖረውና ካንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በመደበኛ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብተው የተማሩ መሆናቸው ከተረጋገጠ፣ የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል፡፡ ዶ/ር ግሩም ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያቱ፤ ”የተካሄደው እልክ አስጨራሽ ሕጋዊ ፍልሚያ አንድ ውጤት በመሆኑ ተደስቻለሁ” ብሏል፡፡ ጋዜጠኛ ማርቲን እስቺቢዬ፣ የኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሦስት ሳምንታት በላይ ግራ ቀኙን ሲያከራክርና ጉዳዩን ሲመረምር በቆየበት ሰዓት፣ ያንዳንድ እማኞችን የምስክርነት ቃል በችሎቱ ላይ አድምጧል፡፡ በእስታቫንገሮቹ ጠበቆች አማካኝነት ቀርበው ከነበሩትም እማኞች መካከል ዶ/ር ግሩም ዘለቀ፣ የፖለቲካ ሳይንቲስቷ ዶ/ር ሉዊስ ኦለን፣ በኖርዌይ ለስደተኞች የቆመ ድርጅት ተወካይ ሚ/ር ጆን ማርቲንሰን፣ የመንግሥት የኢሚግሬሽን መረጃ ማእከል ተወካይ (Land Info)፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የነበረው የእስዊድኑ ጋዜጠኛ ማርቲን እስቺቢዬ፣ የኦነግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ደገፋ አብዲሳ፣ ጋዜጠኛ ጃፈር አሊ በአካል እችሎቱ ላይ ተገኝተው በግልም ሆነ በጋራ እንዲሁም በሌሎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት አደርሷል የሚሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ እንግልት፣ እስርና ስቃይ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ዳኛው በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ስልክ በመደወል በኢትዮጵያ የኖርዌይ ኤምባሲ ዲፕሎማት የሆኑትን የሚስተር ቶሚ ዎልድን ምስክርነት ለችሎቱ አስደምጠዋል፡፡ ዶ/ር ደገፋ አብዲሳ፣ የኦነግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል 7 ይህ በዶ/ር ግሩም ዘለቀ ወገናዊ ተቆርቋሪነት ተጀምሮ ብዙ ሰብአዊ ደርጅቶችን፣ ፖለቲከኞችን፣ የሃይማኖት ሰዎችን ፣ ጋዜጠኞችን፣ ዓለም አቀፍ የህግ ሰዎችን፣ ታዋቂ ግለሰቦችን፣ ባለጉዳዮቹን ኢትዮጵያውያን ስደተኖችንና ሌሎችንም በብርቱ ያሳተፈ ጉዳይ ፍጻሜው ያማረ ይሆናል የሚል ብርቱ እምነት ያላቸው ወገኖች አሉ፡፡ የሎንደኖቹ ጠበቃ አዳም ዋይዝና ጠበቃ ማት ሞሪያርቲ የእስታቫንገሮቹ ጠበቆች፣ የሎንደኖቹ የ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) ዳይሬክተር ጠበቃ አዳም ዋይዝና ባልደረባቸው ጠበቃ ማት ሞሪያርቲና ዶ/ር ግሩም ድሉ የኛ ይሆናል ይላሉ፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ብይን ለማሰማት ቀጥሮ የያዘው የኦስሎው አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣ በነዚህ ዘጠኝ ለናሙናነት በቀረቡ ወካይ ገገባለጉዳዮች ፈለግ የሌሎችንም ስደተኞች ጉዳይ ይመለከት ይሆናል የሚል ተስፋ አለ፡፡ ምን ጊዜም እንበርታ!

No comments:

Post a Comment