Sunday, 4 May 2014

ይህ መንግስት ባለፉት ኣመታት በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ የኦሮሞ ልጆችን ፈጅቷል። ለዚህም ድርጊቱ እስከ ዛሬ በገዳዮች ላይ የተወሰደ እርምጃ የለም። ዛሬም በማን ኣለብኝነት ጊዲያውን ቀጥሎበታል። የህ እየፈሰሰ ያለው የኦሮሞ ህጻናት ደም በመላ ሃገሪቱ ያሉትንም ህዝቦች በሙሉ ሊያሳስብና ሊያስቆጣ ይገባል። በመሆኑም መላው የኢዮዽያ ህዝቦች ይህ ኣሰቃቂ ድርጊት እንዲቆም ድምጻቸውን ማሰማት ኣለባቸው። በተለይም ተደራጅተው የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን መምረጥ የለባቸውም። ኣንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባዘጋጀው የእሪታ ሰልፍ ላይ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት መስጠት ኣለበት ። የኦሮሞ ህጻናት ሞት የሁሉም ኢትዮዽያውያን ህጻናት ሞት ሆኖ መታየት ኣለበት። ኣንዱ ሲገደል ሌላው ዝም ማለቱ ለገዳዩ መንግስትና ግዲያው እውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል።

የኦሮሞ ወጣቶች ትግል የመብት ትግል እንጂ የሌሎችን መብት
ለመንካት ያለመ አይደለም
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በፍንፊኔ ዙሪያ ያሉትን ከተሞች ወደ ፊንፊኔ (ኣዲስ ኣበባ)
የማጠቃለል ፕላን በመቃወም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። በዚህም በመንግስት
ወታደሮች በርካቶች ዜጎች ተገድለዋል። ይህ ተቃውሞ በቀጥታ ያነጣጠረው መንግስት በወሰደው ህገወጥ
እርምጃ ላይ ነው። ስለዚህ ሌሎች በኦሮሚያ የሚኖሩ ዜጎችን የሚያሰጋ ኣንዳችም ሁኔታ ሊኖር ኣይችልም።
ይልቁንም ማንኛውም በክልሉ የሚኖሩ ህዝቦች ከኦሮሞ ወጣቶችና ህዝብ ጎን ቆመው ኣምባገነኑን መንግስት
መቃወም ኣለባቸው እንጂ ስጋት ሊፈጠርባቸው ኣይችልም። ይህንን ለማለት የቻልኩት በኣምቦ በመንግስት
ሃይሎችና በኦሮሞ ህዝብ መካከል በተከሰተው ግጭት ምክንያት የሌሎች ብሄረሰብ ኣባላት ፈርተው
በየቤተክርስትያኑ ተጠልለዋል የሚል ኣርቲክል በኢትዮሜዲያ ላይ Ambo: A city in a war
zone? በሚል ርእስ የተላለፈውን በማየቴ ነው። በጸሃፊውም እንደተጠቀሰው የተከሰተው ግጭት
ሊይጠቃቸው በተሰማራው የመንግስት ሃይሎች ላይ እንጂ በሌሎች ላይ ምንም ኣይነት ችግር ኣልደረሰም። ይህ
ለወደፊቱም ሊታሰብ የማይችል መሆኑን ሁሉም ኣውቆ በጥይት እየተቆላ ካለው ወገኑ ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ
ጎን እንዲቆምና ይህንን የጋራ ጠላት የሆነውን ኣምባገነን መንግስት መቃወምና ማውገዝ ኣልባቸው። የኦሮሞ
ህዝብ በምንም መልኩ ኣብሮ ኣደጎቹንና ጎረቤቶቹን የሚያጠቃበት ባህልም ሆነ ታሪክ የለውም። በዚህም
መጠርጠርና መፈራት የለበትም።
የኢትዮዽያ መንግስት በሃገሪቷ ህገመንግስት የተፈቀዱትን በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶችን በመጣስ
በኦሮሚያ ክልል ህጋዊ ጥያቄ ያቀረቡትን ተማሪዎች በጠራራ ጸሃይ በጥይት በመፍጀት ላይ መሆኑ በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ነው።
ይህ መንግስት ባለፉት ኣመታት በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ የኦሮሞ ልጆችን ፈጅቷል። ለዚህም ድርጊቱ እስከ ዛሬ በገዳዮች ላይ የተወሰደ
እርምጃ የለም። ዛሬም በማን ኣለብኝነት ጊዲያውን ቀጥሎበታል። የህ እየፈሰሰ ያለው የኦሮሞ ህጻናት ደም በመላ ሃገሪቱ ያሉትንም ህዝቦች
በሙሉ ሊያሳስብና ሊያስቆጣ ይገባል። በመሆኑም መላው የኢዮዽያ ህዝቦች ይህ ኣሰቃቂ ድርጊት እንዲቆም ድምጻቸውን ማሰማት
ኣለባቸው። በተለይም ተደራጅተው የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን መምረጥ የለባቸውም። ኣንድነት
ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባዘጋጀው የእሪታ ሰልፍ ላይ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት መስጠት ኣለበት ። የኦሮሞ ህጻናት ሞት የሁሉም
ኢትዮዽያውያን ህጻናት ሞት ሆኖ መታየት ኣለበት። ኣንዱ ሲገደል ሌላው ዝም ማለቱ ለገዳዩ መንግስትና ግዲያው እውቅና እንደመስጠት
ይቆጠራል። መድረክ ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማት ኣለበት። ተከፋፍለን በመቆማችን በተናጠል እየተጠቃና ነው። ስለዚህ ዛሬ በኦሮሚያ
ክልል ህጻናት ላይ የደረሰው ነገ በሌሎችም የማይደርስበት ምክንያት ስለሌለ ከኣሁኑ መተባበር ያስፈልጋል። በመሆኑም በሃገር ውስጥ
ያለው ህዝብ ወገኑ ከጎኑ እያለቀ በቸልታ ማየት በታሪክ ፊት ያስጠይቃል። እስካሁን በመንግስት ወታደሮች ጥይት እያለቁ ባሉት የኦሮሞ
ህጻናት ያሳዘናቸውና ድምጻቸውን ያሰሙት የዜግነት ሃላፊነታቸውን የተወጡት ሊኮሩ ይገባል። ካልተባበርን ከጥቃት ልንድን ኣንችልም።
ይህ ኣሁን የተፈጠረው ሁኔታ ካላስተበበርንና ይህንን ኣስከፊ ኣገዛዝ ለማስወገድ ካልረዳን ምን ጊዜም ልንተባበር ኣንችልም። በዚህ ላይ
የሃገር ውስጥም ሆኑ ከሃገር ውጭ ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ትልቅ ሃላፊነት ያለባቸው ስለሆነ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት መጀመር
ኣለባቸው የሚል እምነት ኣለኝ።
የኦሮሞ ህጻናት ደም በከንቱ ፈሶ ኣይቀርም።
በቀለ ከስውድን

No comments:

Post a Comment